አዋጆች እና መመሪዎች አዋጆች እና መመሪዎች አዋጆች እና መመሪዎች

የተሻሻለው የጥፋት አይነትና የቅጣት መጠን

1. በአሽከርካሪዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶች እና የጥፋቶቹ እርከን ሀ/ አንደኛ ደረጃ የጥፋት ዝርዝር የጥፋት አይነቶች ዝርዝር ተሽከርካሪ ያለአግባብ የጎተተ 2 የግጭት መከላከያ ቆብ (ሄልሜት) ሳያደርግ ወይም አድርጎ ሳያስር ብስክሌት የነዳ ወይም የብስክሌቱን መሪ በእጁ ሳይዝ የነዳ 3 በተሽከርካሪው ውስጥ የተሟላ የመጀመሪያ ዕርዳታ መስጫ ኪት እና የሚሰራ የድንገተኛ እሳት ማጥፊያ መሳሪያ ሳይኖረው የንግድ ተሽከርካሪ ያሽከረከረ የሚበኑ ወይም የሚበተነ ነገሮችን ያለአግባብ ጭኖ ያሽከረከረ …
Read More

የመንጃ ፈቃድ /የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ/ ምድብና ለማሽከርከር የሚያስችለን የተሽከርካሪ አይነቶች

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ምድብ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለማሽከርከር የሚያስችል የሸከርካሪ አይነት 1 የሞተርሳይክል የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ | ፈቃድ ምድብ ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ተሽከርካሪ 2 የባለ ሶስት እግር የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ | ፈቃድ ምድብ ማንኛውም የባለ ሶስት እግር ባለሞተር ተሽከርካሪ 3 የአውቶሞቢል የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ምድብ እስከ ስምንት /8/ መቀመጫ ያለው …
Read More

አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት

አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት ነጻ የስልክ መስመር የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ 9417 የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ 696 የአሽከርካሪ ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን 7766 የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት 8981
Read More

የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር አደረጃጀትና ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ

የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች የአደረጃጀት ብቃት ማረጋገጫና የአፈፃፀም መመሪያ ተሻሽሎ መዘጋጀቱን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታውቋል።  የተሻሻለው መመሪያ በጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ኦፕሬተሮችን ውስጣዊ አሠራር ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።
Read More

awaj.png

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ

የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች የአደረጃጀት ብቃት ማረጋገጫና የአፈፃፀም መመሪያ ተሻሽሎ መዘጋጀቱን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታውቋል።  የተሻሻለው መመሪያ በጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ኦፕሬተሮችን ውስጣዊ አሠራር ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።
Read More

መምሪያዎች

የከተማ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት አገልግሎት የዲሲፕሊን አፈጥጻጸም መመሪያ 2009

የከተማ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት አገልግሎት የዲሲፕሊን አፈጥጻጸም መመሪያ 2009

የከተማ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት አገልግሎት የዲሲፕሊን አፈጥጻጸም መመሪያ 2009
Read More

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር (Proclamation No.107/2018)

አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፸፬/፪ሺ፲ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አዋጅ

በሰው ህይወትና በንብረት ላይ እየደረሰ ላለው የመንገድ ትራፊክ አደጋ አንዱና ዋነኛው መንስኤ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት
Read More

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አሰራር መመሪያ 01/2007

ኢኤስኤም› በህዳር በ2003 ዓ.ም ዓ.ም የመጀመሪያውን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አሰራር መመሪያ አውጥቶ ለሁሉም ክልል አሰራጭቶ እንደነበር ይታወቃል ከ2004 እስከ 200 6ዓ.ም የተተገበረውን መመሪያበትግበራው ወቅት የታዩ ክፍተቶችን መሰረት በማድረግ የተሻሻለውንና የቀድሞእንዲሁምሊተካ የሚችል በማድረ
Read More

የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነትጻ እንዲሆኑ ለማድረግ የወጣ መመሪያ

“ታክ ሲ” ማለ ት በ ከ ተሞች ውስ ጥ የ ትራን ስ ፖር ት አ ገ ልግ ሎት የ ሚሰ ጥ ሾ ፌሩን ጨምሮ ከ አ ራት እ ስ ከ10 መቀ መጫ ያ ለ ው ተሽ ከ ር ካ ሪ ነ ው 2/ “ሙሉ በ ሙሉ የ ተበ ታተነ (Complete Knocked Down)”ማለ ትየ ን ግድና ኢን ዱስ ትሪሚኒ ስ ቴር የ ሚያ ወጣውን መስ ፈር ት በ ሚያ ሟላ ሁኔ ታ ወደአ ገ ር የ ሚገ ባ ተሽ ከር ካ ሪ ነ ው
Read More

የግምት ታክስ ስሌት አፈፃፀም መመሪያ 2010

የግምት ታክስ ስሌት አፈፃፀም መመሪያ 2010 በዝርዝር
Read More

የእጩ አሽከርካሪዎች፤ ማሠልጠኛ ተቋማት፤ አሠልጣኞች እና ሠልጣኞች የሥ-ምግባር መመሪያ 2010

የእጩ አሽከርካሪዎች፤ ማሠልጠኛ ተቋማት፤ አሠልጣኞች እና ሠልጣኞች የሥ-ምግባር መመሪያ 2010 በዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቦል፡፡
Read More

የትራፊክ የቅጣት እርከን

1 እርከን የጥፋት ዝርዝሮች

1. ተሽከርካሪን ያለአግባብ የጎተተ
2. የየግጭት መከላከያ ቆብ (ሄልሜት) ሳያደርግ ወይም አድርጎ ሳያስር ብስክሌት የነዳ ወይም የብስክሌቱን መሪ በእጁ ሳይዝ የነዳ
3. በተሽከርካሪው ውስጥ የተሟላ የመጀመሪያ ዕርዳታ መስጫ ኪት እና የሚሰራ የድንገተኛ እሳት ማጥፊያ መሳሪያ ሳይኖረው የንግድ ተሽከርካሪ ያሽከረከረ

4. የሚበኑ ወይም የሚበተኑ ነገሮችን ያለአግባብ ጭኖ ያሽከረከረ

5. ጭነትን እያፈሰሰ ወይም እየጣለ ያሽከረከረ ወይም ያፈሰሰውን ወይም የጣለውን ጭነት ሳይጠርግ ወይምእንዲጠረግ ሳያደርግ ጉዞውን የቀጠለ አሽከርካሪ

6. በትራፊክ መብራት ላይ ወይም በመስቀለኛ መንገድ ላይ በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ የሰጠ ወይም ግብይት ያደረገ

7. ሲጋራ እያጨሰ ያሽከረከረ

8. የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ተሽከርካሪን የአደጋ አገልግሎት ስራ ላይ ሳይሆን አላግባብ የተፈቀደለትን የድምጽና የአደጋ ምልክት መብራት በመጠቀም ያሽከረከረ

9. ከ13 አመት በታች የሆነን ሕጻን ከአሽከርካሪው ጎን በሚገኘው የተሽከርካሪው ክፍል (ጋቢና) ውስጥ አስቀምጦ ያሽከረከረ

10. ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ የመንገድ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ድጋፍና ጥንቃቄ ሳያደርግ ያሽከረከረ አሽከርካሪ

2 እርከን የጥፋት ዝርዝሮች

1 የተሟላ የጭነት ማቀፊያ /ስፓንዳ/ ሳይኖረው ጭነት ጭኖ ያሽከረከረ
2 የጥሩምባ ድምጽ ያለአግባብ ወይም በተከለከለ ቦታ ላይ የተጠቀመ ወይም ተገቢ ባልሆነ የማስጠንቀቂያ (የጥሩንባ) ድምጽ የተጠቀመ
3 በመንገድ ላይ ተሽከርካሪ ያጠበ ወይም እንዲታጠብ ያደረገ

4. በአውቶቡስ ማቆሚያ ስፍራ ላይ፣ በእግረኛ መንገድ ላይ፣ በትራፊክ ምልክት ወይም መብራት አጠገብ፣ በተሽከርካሪ
መግቢያ ወይም መውጫ በር ላይ፣ ሌላ ተሽከርካሪ ደርቦ፣ ወይም በመንገድ ምልክት አማካኝነት ማቆም በተከለከለበት
ማናቸውም ስፍራ ላይ ተሽከርካሪ ያቆመ

5. የአሽከርካሪውን ዕይታ የሚከለክል መጋረጃ፣ ተለጣፊ ላስቲክ ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን በተሽከርካሪው ላይ
ያስቀመጠ ወይም የለጠፈ
6. በተፈቀደው ፍጥነት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ

7. ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም በጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ
8. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ
9. በሕግ በተፈቀደው ርቀት ምልክት ሳያሣይ የተጠመዘዘ፣ አቅጣጫ የቀየረ፣ ተሽከርካሪ የቀደመ ወይም
ተሽከርካሪ ያቆመ
10. በመንገድ ላይ ያለን ውሀ በተሽከርካሪው አማካኝነት በእግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ
11. የትራፊክ ምልክት ወደ ቀኝ ብቻ መታጠፍ በሚፈቅድ መንገድ ላይ መንገድ የዘጋ
12. በተከለከለ ቦታ ላይ ወይም የመንገዱን ቀኝ ዳር ሳይዝ ተሳፋሪ ወይም ዕቃ የጫነ ወይም ያወረደ
13. በማብሪያ ጊዜ መብራት እያለው ሳያበራ ያሽከረከረ
14. በጠባብ መንገድ ላይ ወይም በመታጠፊያ መንገድ በ12 ሜትር ውስጥ ተሽከርካሪ ያቆመ
15. ለእግረኛ ወይም ተላላፊ ቅድሚያ ያልሰጠ
16. ቅድሚያ መስጠት ላለበት ተሽከርካሪ ቅድሚያ ያልሰጠ
17. በትራፊክ ደሴት ላይ ያሽከረከረ ወይም የመንገድ አከፋፋይ ደሴትን /መስመርን/ በማቋረጥ ያሽከረከረ
18. ከተፈቀደለት ጊዜ በላይ የተበላሸ ተሽከርካሪን መንገድ ላይ ያቆመ ወይም አቁሞ የጠገነ
19. የሚታጠፍበትን አቅጣጫ ሳይዝ ወይም ደርቦ የታጠፈ
20. ሁለት መስመር ባለው መንገድ ላይ በቀኝ በኩል ተሽከርካሪ የቀደመ
21. ምልክት ሳያሳይ ተሽከርካሪ ያቆመ ወይም ከቆመበት ቦታ ያንቀሳቀሰ
22. ለአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ቅድሚያ ያልሰጠ
23. ወደ የማይሄድበት አቅጣጫ ምልክት ያሳየ
24. ከሚገባው በላይ ጭስ እያጨሰ ወይም ዘይት ወይም ነዳጅ እያፈሰሰ የሚሄድ ተሽከርካሪን ያሽከረከረ
25. ከሰባት ዓመት በታች የሆነ ህጻንን ለደህንነቱ ሲባል በተሰራው ማቀፊያ ውስጥ ሳያስቀምጥ ያሽከረከረ
26. የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት
ሳይቆም የሄደ
27. በተራፊ ጭነት ላይ ተገቢውን ምልክት ሳያደርግ ወይም በተሽከርካሪው ላይ የተጫነውን ጭነት በሚገባ ሳያስር
ወይም ሳይሸፍን ያሽከረከረ
28. በእግረኛ ማቋረጫ መንገድ ላይ ወይም ከእግረኛ ማቋረጫ በአስራ ሁለት (12) ሜትር ውስጥ ተሽከርካሪ ያቆመ
29. የእሳት አደጋ ተሽከርካሪ ውሃ መሙያ ቦታ ላይ ወይም በእሳት አደጋ መከላከያና በሆስፒታል መግቢያና
መውጪያ በር ላይ ተሽከርካሪ ያቆመ፧
30. ባልተፈቀደ ቦታ ወይም ባልተወሰነ ሰዓት ወይም የለማጅ ምልክት ሳይለጥፍ አሽከርካሪ ማሽከርከር
ያስተማረ ወይም ያለማመደ
31. የተሽከርካሪው በር ተከፍቶ እያለ ወይም ጨርሶ ሳይዘጋ ያሽከረከረ
32. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት የሚያሽከረክረውን ተሽከርካሪ ፈቃድ ለሌለው ወይም
በዚህ ደንብ መሰረት ለታገደበት ሰው አሳልፎ የሰጠ
33. ተሽከርካሪው በእንቅስቃሴ ላይ እያለ ተሳፋሪ የጫነ ወይም ያወረደ
34. ባለ ሦስት ጎን አንጸባራቂ ምልክት በበቂ ርቀት ሳያስቀምጥ የተበላሸ ተሽከርካሪ ያቆመ
35. ከተፈቀደለት ጊዜ በላይ በማዘግየት ተሽከርካሪን በመንገድ ላይ ያቆመ
36. ተሸከርካሪውን ያለአግባብ ወደ ኋላ ያሽከረከረ
37. የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ተሽከርካሪ በ100 ሜትር ርቀት ተከትሎ ያሽከረከረ
38. በተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራ ወይም በመንገድ ላይ ተሽከርካሪ የጠገነ

3 እርከን የጥፋት ዝርዝሮቹ

1. የጉዞ ረድፉን ወይም መስመሩን ሳይጠብቅ ያሽከረከረ
2. የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጃ መሙላት
3. ከተሽከርካሪው የመጫን አቅም በላይ ትርፍ ሰው የጫነ
4. በምድቡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ከተፈቀደለት ደረጃ በላይ የሆነ ተሽከርካሪን ያሽከረከረ

5. ተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ ወይም መልእከት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ
6.
የጭንቅላት መከላከያ (ሄልሜት) ሳያደርግ ወይም አድርጎ ሳያስር ወይም አብሮት የጫነው ሰው
ማድረጉንና ማሰሩን ሳይረጋግጥ ሞተር ሳይክል ያሽከረከረ
7.
በጭነት ተሽከርካሪ በሕግ ከተፈቀደለት ውጪ ሰውን ያሳፈረ
8.
በማብሪያ ጊዜ መብራት ሣይኖረው ያሽከረከረ
9.
ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ
10.
የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ

11. ቀይ የትራፊክ መብራት የጣሰ
12. በተከለከለ መንገድ ወይም አቅጣጫ ያሽከረከረ
13. የትራፊክ ክብ ደሴትን በግራ ያቋረጠ
14. በድልድይ ላይ ተሽከርካሪ ያቆመ
15. ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ
16. በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው ለሚገባ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ያልሰጠ
17. በሕግ ከተፈቀደው ከፍታ፣ ርዝመት፣ እና ስፋት ውጭ ጭነት የጫነ
18. የመለያ ሠሌዳ ቁጥሩ ሊታይ የማይችል ቦታ ላይ ያሰረ ወይም የተደመሰሰ ወይም የተቆረጠ
ወይም የተሸፈነ ወይም የተለያዩ ቀለማትን የቀባ ተሸከርካሪን ያሽከረከረ
19. ተሽከርካሪው የፊት ወይም የኋላ ሠሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ
20. የተላላፊ ሠሌዳ ከተፈቀደለት ጊዜና ቦታ ውጪ የተጠቀመ
21. ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ጭነትን ከሕዝብ ጋር የጫነ
22. ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ የተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ
23. በተሽከርካሪው የውጭ አካል ላይ ሰው የጫነ
24. ከተሽከርካሪው የመጫን አቅም በላይ ትርፍ ሰው የጫነ 1500 ብር እና በጫነው በእያንዳንዱ
ትርፍ ለተጫነ ሰው ተጨማሪ 100 ብር ይቀጣል
25. በጭነት ተሽከርካሪ በተፈቀደው አግባብ ካልሆነ በስተቀር በተሽከርካሪው የውጭ አካል ሰውን
ያሳፈረ 1500 ብር እና በጫነው በእያንዳንዱ ትርፍ ለተጫነ ሰው ተጨማሪ 100 ብር ይቀጣል

 

4 ልዩ ደረጃ ጥፋቶች

1.ተሸከርካሪ በማሽከርካር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም አሽከርካሪ
2. በተሽከርካሪው ማናቸውንም አይነት ጥፋት በመፈፀም በሰው አካል ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ያደረሰ አሽከርካሪ
3. በተሽከርካሪው ማናቸውንም አይነት ጥፋት በመፈፀም በሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰ
4. በተሽከርካሪው ማናቸውንም አይነት ጥፋት በመፈፀም በሰው ላይ ሞት ያደረሰ

5.ግልፅ የሆነ ደንብ ወይም መመሪያ በመተላለፍ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሞት ጉዳት ያደረሰ
6. የአልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ 0.24-0.6 ሚሊግራም/ሊትር
7. የአልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ 0.61-0.8 ሚሊግራም/ሊትር
8.የአልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ከ0.81-1.0 ሚለ, ግራም/ሊትር
9 . የአልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ
10. ወጣት አሽከርካሪዎች ፣ ጀማሪ _ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተርሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት
የጫኑ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውምመጠን ከተገኘ
11. ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ እስከ አምስት ኪ/ሜ በሰዓት
12. ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ6-10ኪ/ሜ በስዓት ሲበልጥ
13. ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ11-20ኪ/ሜ በስዓት ሲበልጥ
14. ከተፈቀደፍጥነትበላይበ21-30ኪ/ሜበስዓትሲበልጥ
15. ከተፈቀደፍጥነትበላይበ31-40ኪ/ሜበስዓትሲበልጥ
16. ከተፈቀደፍጥነትበላይከ41ኪ/ሜበስዓትሲበልጥ
17. ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ50ኪ/ሜ እና ከዛ በላይ በስዓት ሲበልጥ
18.የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ፤ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰውወደህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ
19. የአሽከርካሪ  ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ
20. አፈር ፣ አሸዋ ፣ ድንጋይና ተመሳሳይነ ገሮችን የሚመለከተውን አካል ሳያስፈቀድ በተሸከርካሪ ወይም በእግረኛ መንገድ ላይ ያራገፈ አሽከርካሪ
21. ያበላሸውን መንገድ መጠገኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሰንሰለት የሚሽከረከር ልዩ ተንቀሳቃሽበ መንገድ ላይ ያሽከረከረ
22. ፍጥነት የሚያዛባ ቴክኖሎጅ በመጠቀም ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ
በሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር ያደናቀፈ
23. አፈር ፣ አሸዋ ፣ ድንጋይና ተመሳሳይ ነገሮችን የሚመለከተውን አካል ሳያስፈቀድ በተሸከርካሪ ወይም በእግረኛ መንገድ ላይ ያራገፈ አሽከርካሪ

5 ሌሎች የድንብ መተላለፍ

1. በማብሪያ ጊዜ በጉልህ የሚታይ መብራት ሳይዝና ለተሸከርካሪው አቅራቢያ በሆነው ጎን መብራቱን ሳያሳይ እንስሳትን የነዳ ማንኛውም የእንስሳት ጠባቂ
2. ከማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች ወይም ከተፈቀደላቸው ሰዎች በስተቀር በተሸከርካሪ መንገድ ላይ በእጅ የሚገፋ ባለ መንኩራኩር ወንበርን ወይም የሚሳብ ጋሪን የገፋ ወይም የሳበ ማንኛውም ሰው
3. ለመጫወቻ እና ለጊዜ ማሳለፊያ ተብሎ የተሰራ ብስክሌት ወይም በጫማ መልክ የሚጠለቅ ተንሸራታች ወይም ሌሎች መጫወቻዎችን በተሸከርካሪ መንገድ ላይ ወይም የተጠቀመ ማናቸውም ሰው፡፡

4. በብስክሌት ላይ የተዘጋጀው መቀመጫ ላይ ተመቻችቶ ሳይቀመጥ ወይም የብስክሌቱ
መሪ በሁለት እጁ ሳይዝ እና በእግሮቹም መርገጫውን ሳይረግጥ ብስክሌት የነዳ ማንኛውምሰው
5. ብስክሌት በሚያሽከረክርበት ጊዜ በማናቸውም አኳኋን በመጓዝ ላይ ያለሌላን ተሸከርካሪ ወይም ሌላን ብስክሌት ይዞ የነዳ ማንኛውም ሰው
6. በመንገድ ላይ እንስሳትን የነዳ ወይም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው
7. በተሸከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ 
ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሸከርካሪ ባለንብረት
8. በሀዘን ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳይኖረው የተሸከርካሪዎችን ወይም የእግረኞችን እንቅስቃሴ የሚያውክ ቁሳቁስ ወይም ሽቀጥ
በእግረኛ ወይም በተሸከርካሪ መንገድ ላይ ያስቀመጠ ፣ የተከለ ፣ የንግድ ስራ የሰራ ወይም ተመሳሳይ ነገሮች ያከናወነ ማንኛውም ሰው፡፡
9. በማብሪያ ጊዜ በጉልህ የሚታይ መብራት ሳይዝ እና ለተሽከርካሪው አቅራቢያ በሆነው ጎን መብራቱን ሳያሳይ እንስሳት የነዳ ማንኛውም የእንስሳት ነጋዴ 

10.  ማንኛውም የመንገድ ምልክት ያነሳ ወይም ያበላሸ ወይም ከቆመበት ያዛወረ ወይም የለወጠ ወይም በማንኛውም አኳኋን እንዳይታይ ወይም እንዳይታወቅ
ያደረገ ማንኛውም ሰው
11. ያበላሸውን መንገድ መጠገኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ያለ ፈቃድ ተሸከርካሪ ወይም እግረኛ መሄጃ መንገድን የቆፈረ ፣ ያበላሸ ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን
ያከናወነ ማንኛውም ሰው
12. ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሸከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት
ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት
13. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው
14, የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሸከርካሪ በማሽከርካር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረ ሰማንኛውም ሰው
15. ከፖሊስ በተሸከርካሪው ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልፅ የፅሁፍ በወንጀል ህጉ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገናውን ያከናወነ ጋራዥ/የጋራዥባለቤት/
16. አመታዊ የተሸከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሸከርካሪ ባለንብረት

6 እግረኞች ስለሚቀጡበት

1. ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርግ መንገድ ያቋረጠ
2. ለተሸከርካሪ የተፈቀደ መንገድ ላይ ያለ በቂ ምክንያት የቆመ ወይም የተጓዘ
3. እግረኛ መንገድ በሌለበት መንገድ ቀኝ ጠርዙን ይዞ የተጓዘ
4. ለእግረኛ መንገድ ተብሎ ከተከለለ መንገድ ውጭ የተጓዘ

5. በብረትም ሆነ በግንብ ተለይተው የታጠሩ መንገዶች ዘሎ መንገድ ያቋረጠ
6. በጆሮ ማዳመጫ የተለያዩ ድምፆችን እያዳመጠ መንገድ ያቋረጠ
7. ለእግረኛ ክልክል ነው የሚልምልክት ባለበት መንገድ ወይም እግረኛ እንዳያቋርጥ 
በተከለከለበት የማሳለጫ ወይም የቀለበት መንገድ ያቋረጠ
8. ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 ካሉት ጥፋቶች አንዱን ፈፅሞ
ክፍያ መፈፀም ያልቻለ ወይም ያልፈለገ ማንኛውም ሰው ተመጣጣኝ የሆነ ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል

  1. የትራፊክ ቁጥጥር ተግባሩን ሲያከናውን ለመንገድ ተጠቃሚዎችና  ለደንብ ተላላፊዎች ሙያው የሚጠይቀውን ተገቢውን አክብሮት ያላሳየ ፣ ያመናጨቀ ወይም የተሳደበ በማንኛውም ምክንያት አድሎ ሆኖ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የፈፀመ በዚህ ደንብ ከተደነገገው ውጭ በተለይም ጥፋተኛ ባልሆነ  የመንገድ ተጠቃሚ ላይ አላግባብ የደንብ መተላለፍ ቅጣት የወሰነ እንደሆነ
  2.  ጉቦ የተቀበለ ወይም የጠየቀ እንደሆነ ወይም በአንድ አመት ጊዜ  ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር አንድ ከተገለፁት ጥፋቶች አንዱን በድጋሚ እና በዲሲፕሊን የሚጠየቅ
    የፈፀመ እንደሆነ

የተሻሻለው የትራፊክ ደንብ መተላለፍ ቅጣት

ሀ. ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋት ሲፈፀም

ተ.ቁ የጥፋቱ እርከን ለጥፋቱ የሚመዘገብ ነጥብ ለጥፋቱ የሚከፈል የገንዘብ ቅጣት መጠን/ እርምጃ
1 1ኛ የጥፋት እርከን 1 500.00 ብር
2 2ኛ የጥፋት እርከን 2 1000.00 ብር
3 3ኛ የጥፋት እርከን 3 1500.00 ብር
4 ልዩ ደረጃ ጥፋት 8-21 ለተለያዩ ደረጃ ያላቸው እገዳዎች እና የገንዘብ ቅጣቶች
5 ሌሎች የደንብ መተላለፎች 0 ከ 100 - 20000 ብር
6 በእግረኞች ስለሚፈጽሙ ጥፋቶች 0 100 - 150 ብር
7 በትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስለሚፈጽሙ ጥፋቶች 0 -

ለ. ለሁለተኛ ጊዜና ከሁለተኛ ጊዜ በላይ ጥፋት ሲፈፅም

ተ.ቁ ለጥፋቱ የሚመዘገብ ነጥብ ለጥፋቱ የሚከፈል የገንዘብ ቅጣት መጠን/ እርምጃ
1 2 – 4 600.00 ብር
2 5 – 7 850.00 ብር
3 8 – 10 1600.00 ብር
4 11 – 13 2000.00 ብር
5 14 – 16 ለ6 (ስድስት) ወር የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶ በአገልግሎቱ ወይም በሚመለከተው ህጋዊ አካል የሚሰጠውን የዕውቀትና ክህሎት ስልጠና ወስዶ እና የማሽከርከር ብቃቱ ተረጋግጦ ፈቃዱን መልሶ ማግኘት ይችላል።
6 17-20 የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ለአንድ አመት ታግዶ ከቆየ በኋላ በአገልግሎቱ ወይም በሚመለከተው ህጋዊ አካል የሚስጠውን የዕውቀትና ክህሎት ስልጠና ወስዶ እና የማሽከርከር ብቃቱ ተረጋግጦ ፈቃዱን መልሶ ማግኘት ይችላል፡፡
7 ከ21 በላይ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ለአንድ አመት ከሰድስት ወር ታግዶ ከቆየ በኋላ በአገልግሎቱ ወይም በሚመለከተው ህጋዊ አካል የሚስጠውን የዕውቀትና ክህሎት ስልጠና ወስዶ እና የማሽከርከር ብቃቱ ተረጋግጦ ፈቃዱን መልሶ ማግኘት ይችላል፡፡

ሐ. ቅጣትን በወቅቱ አለመፈፀምና የሚያስከትለው ተጨማሪ ቅጣት

ተ.ቁ ቅጣቱ የሚፈፀምበት ጊዜና የሚጣል ተጨማሪየገንዘብ ቅጣት መጠን ተጨማሪ የነጥብ ቅጣት
1 10ኛው ቀን ድረስ ቅጣቱን የሚፈፅም የተጣለበትን የቅጣት መጠን ብቻ ከፍላል 0
2 ከ 11 ቀን በኋላ ቅጣቱ የሚፈፀም ሰው ከ 11ኛ ቀን ጀምሮ ላሉት እያንዳንዱ ቀናት የቅጣቱ መጠን 5% እየተጨመረ ይቀጣል 1

መ/ ልዩ ደረጃ ጥፋት

ተ.ቁ የጥፋት አይነቶች ቅጣት የሚመዘገብ ነጥብ
1 ተሸከርካሪ በማሽከርካር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም አሽከርካሪ 1600 ብር 8
2 በተሸከርካሪው ማናቸውንም አይነት ጥፋት በመፈፀም በሰው አካል ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ያደረሰ አሽከርካሪ ለስድስት ወር ይታገዳል 14
3 በተሸከርካሪው ማናቸውንም አይነት ጥፋት በመፈፀም በሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰ ለአንድ አመት እገዳ 17
4 በተሸከርካሪው ማናቸውንም አይነት ጥፋት በመፈፀም በሰው ላይ ሞት ያደረሰ ለአንድ አመት እገዳ 17
5 ግልፅ የሆነ ደንብ ወይም መመሪያ በመተላለፍ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሞት ጉዳት ያደረሰ ለአንድ አመት ከስድስት ወር እገዳ 21
6 የአልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ 0.24-0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር 3
7 የአልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ 0.61-0.8 ሚሊግራም/ሊትር 2000 ብር 3
8 የአልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ከ 0.81-1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2000 ብር 8
9 የአልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ 3000 ብር 8
10 ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች፣ የንግድ ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2000 ብር 8
11 ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ እስከ አምስት ኪ/ሜ በሰዓት 0 0
12 ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ 6-10 ኪ/ሜ በስዓት ሲበልጥ 1500 ብር 3
13 ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ 11-20 ኪ/ሜ በስዓት ሲበልጥ 1700 ብር 3
14 ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ በ 21-30 ኪ/ሜ በስዓት ሲበልጥ 1800 ብር 3
15 ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ በ 31-40 ኪ/ሜ በስዓት ሲበልጥ 2000 ብር 8
16 ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ 41 ኪ/ሜ በስዓት ሲበልጥ 2500 ብር 8
17 ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ ከ 50 ኪ/ሜ እና ከዛ በላይ በስዓት ሲበልጥ 3500 ብር 8
18 የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ፤ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል 21
19 የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶ በት ሳለ ያሽከረከረ 3000 ብር 8
20 አፈር፣ አሸዋ፣ ድንጋይ ና ተመሳሳይ ነገሮችን የሚመለከተውን አካል ሳያስፈቀድ በተሸከርካሪ ወይም በእግረኛ መንገድ ላይ ያራገፈ አሽከርካሪ 3000 ብር 8
21 ያበላሸውን መንገድ መጠገኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሰንሰለት የሚሽከረከር ልዩ ተንቀሳቃሽ በመንገድ ላይ ያሽከረከረ 7000 ብር 8
22 ፍጥነት የሚያዛባ ቴክኖሎጅ በመጠቀም ከተፈቀደ ፍጥነት በላይ በሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር ያደናቀፈ 10,000 ብር የገንዘብ ቅጣት እና ተሸከርካሪው ላይ የተገጠመውን ሀገወጥ አደናቃፊ መሳሪያ መውረስ 11
23 አፈር፣ አሸዋ፣ ድንጋይ ና ተመሳሳይ ነገሮችን የሚመለከተውን አካል ሳያስፈቀድ በተሸከርካሪ ወይም በእግረኛ መንገድ ላይ ያራገፈ አሽከርካሪ 3000 ብር 8

ሠ/ ሌሎች የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች

ተ.ቁ የጥፋት አይነቶች ቅጣት
1 በማብሪያጊዜበጉልህየሚታይመብራትሳይዝናለተሸከርካሪያበሆነው ጎንመብራቱንሳያሳይእንስሳትንየነዳማንኛውምየእንስሳትጠባቂ 100 ብር
2 ከማዘጋጃቤትሰራተኞችወይምከተፈቀደላቸውሰዎችበስተቀርበተሸከርካሪ መንገድላይበእጅየሚገፋለመንኩራኩርወንበርንወይምየሚሳብጋሪንየገፋ ወይምየሳበማንኛውምሰው 100 ብር
3 ለመጫወቻእናለጊዜማሳለፊያተብሎየተሰራብስክሌትወይምበጫማመልክ የሚጠለቅተንሸራታችወይምሌሎችመጫወቻዎችንበተሸከርካሪመንገድላይ ወይምየተጠቀመማናቸውምሰው፡፡ 100 ብር
4 በብስክሌትላይየተዘጋጀውመቀመጫላይተመቻቶሳይቀመጥወይምየብስክሌቱ መሪበሁለትእጁሳይዝእናበእግሮቹምመርገጫውንሳይረግጥብስክሌትየነዳ ማንኛውምሰው 100 ብር
5 ብስክሌትበሚያሽከረክርበትጊዜበማናቸውምአኳኋንበመጓዝላይያለሌላን ተሸከርካሪወይምሌላንብስክሌትይዞየነዳማንኛውምሰው 100 ብር
6 በመንገድላይእንስሳትንየነዳወይምይዞየተገኘማንኛውምሰው 200 ብር
7 በተሸከርካሪላይተገቢያልሆነአካልየጨመረወይምከተፈቀደትናበርውጭ ተጨማሪወይምበተሸከርካሪመንገድላይ ወይምየተጠቀመማናቸውምሰው፡፡ 400 ብር
8 በሀዘንምክንያትካልሆነበስተቀርከሚመለከተውአካልፍቃድሳይኖረው የተሸከርካሪዎችንወይምየእግረኞችንእንቅስሃሴየሚያውክቁሳቁስወይምሽቀጥ በእግረኛወይምበተሸከርካሪመንገድላይያስቀመጠ፣የተከለ፣የንግድስራየሰራ ወይምተመሳሳይነገሮችያከናወነማንኛውምሰው፡፡ 5,000 ብር
9 በማብሪያጊዜበጉልህየሚታይመብራትሳይዝእናለተሸከርካሪውአቅራቢያ በሆነውጎንመብራቱንሳያሳይእንስሳትየነዳማንኛውምየእንስሳትነጋዴ 500 ብር
10 ማንኛውምየመንገድምልክትያነሳወይምያበላሸወይምከቆመበትያዛወረ ወይምየለወጠወይምበማንኛውምአኳኋንእንዳይታይወይምእንዳይታወቅ ያደረገማንኛውምሰው 1000 ብር
11 ያበላሸውንመንገድመጠገኑእንደተጠበቀሆኖያለፈቃድተሸከርካሪወይም እግረኛመሄጃመንገድንየቆፈረ፣ያበላሸወይምሌሎችተመሳሳይነገሮችን ያከናወነማንኛውምሰው 3000 ብር
12 ከባለቤትነትወይምበይዞታውየተያዘውንተሸከርካሪየአሽከርካሪብቃት ማረጋገጫፈቃድለሌላውሰውአሳልፎየሰጠማንኛውምየተሸከርካሪ ባለንብረት 3000 ብር
13 የአሽከርካሪብቃትማረጋገጫፈቃድሳይኖረውተሸከርካሪያሽከረከረ ማንኛውምሰው 5000 ብር
14 የአሽከርካሪብቃትማረጋገጫፈቃድሳይኖረውተሸከርካሪበማሽከርካር በንብረትላይጉዳትያደረሰማንኛውምሰው 7000 ብር
15 ከፖሊስበተሸከርካሪውላይየደረሰውንየጉዳትአይነትየሚገልፅየፅሁፍ ማስረጃሳይቀበሉጥገናውንያከናወነጋራዥ/የጋራዥባለቤት/ በወንጀልህጉ የሚያስጠይቀው እንደተጠበቀሆኖ 20,000 ብር ይቀጣል
16 አመታዊየተሸከርካሪምርመራያላደረገየተሸከርካሪባለንብረት 3000 ብር

ረ/ እግረኞች ስለሚቅጡበት

ተ.ቁ የጥፋቶች ዝርዝር ቅጣት
1 ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርግ መንገድ ያቋረጠ 100 ብር
2 ለተሸከርካሪ የተፈቀደ መንገድ ላይ ያለበቂ ምክንያት የቆመ ወይም የተጓዘ 100 ብር
3 እግረኛ መንገድ በሌለበት መንገድ ቀኝ ጠርዙን ይዞ የተጓዘ 100 ብር
4 ለእግረኛ መንገድ ተብሎ ከተከለለ መንገድ ውጭ የተጓዘ 100 ብር
5 በብረትም ሆነ በግንብ ተለይተው የታጠሩ መንገዶች ዘሎ መንገድ ያቋረጠ 150 ብር
6 በጆሮ ማዳመጫ የተለያዩ ድምፆችን እያዳመጠ መንገድ ያቋረጠ 150 ብር
7 ለእግረኛ ክልክል ነው የሚል ምልክት ባለበት መንገድ ወይም እግረኛ እንዳያቋርጥ በተከለከለበት የማሳለጫ ወይም የቀለበት መንገድ ያቋረጠ 150 ብር
8 በዚህ ሰንጠረዥ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 ካሉት ጥፋቶች አንዱን ፈፅሞ ክፍያ መፈፀም ያልቻለ ወይም ያልፈለገ ማንኛውም ሰው ተመጣጣኝ የሆነ ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል

የትራፊክ ተቆጣጣሪ ጥፋቶች

ተ.ቁ የጥፋቶች ዝርዝር ቅጣት
ተ.ቁ የጥፋት አይነት የሚወሰድ እርምጃ
1 የትራፊክ ቁጥጥር ተግባሩን ሲያከናውን ለመንገድ ተጠቃሚዎችና ለደንብ ተላላፊዎች ሙያው የሚጠይቀውን ተገቢውን አክብሮት ያላሳየ፣ ያመናጨቀ ወይም የተሳደበ፣ በማንኛውም ምክንያት አድሎ ሆኖ በዚህ ደንብ ከተደነገገው ውጭ በተለይም ጥፋተኛ ባልሆነ የመንገድ ተጠቃሚ ላይ አላግባብ የደንብ መተላለፍ ቅጣት የወሰነ እንደሆነ አግባብነት ባለው ህግ በዲሲፕሊን የሚጠየቅ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡
2 ጉቦ የተቀበለ ወይም የጠየቀ እንደሆነ ወይም በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር አንድ ከተገለፁት ጥፋቶች አንዱን በድጋሚ የፈፀመ እንደሆነ አግባብነት ባለው ሀግ በወንጀል እና በዲሲፕሊን የሚጠየቅ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከትራፊክ ተቆጣጣሪነት ሀላፊነቱ እንዲነሳ ይደረጋል፡፡
error:
All in one
Scroll to Top