3/ ፈቃድ ሰጭው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ
(2) መሠረት ማመልከቻ ሲቀርብለት አመልካቹ
ተገቢውን ክፍያ እንዲፈጽም ካስደረገ በኋላ ምትክ
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰጠዋል
4/ ምትክ የተሰጠበትን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃድ መልሶ ያገኘ ሰው ተጨማሪ የሆነው ፈቃድ
እንዲሰረዝና እንዲወገድ ወዲያው ለፈቃድ ሰጭው
አካል ማስረከብ አለበት
፲፱. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ፀንቶ
ስለሚቆይበት ጊዜና ስለማሳደስ
1/ ማንኛውም ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃድ ፀንቶ የሚቆየው ከተሰጠበት ቀን አንስቶ
ለአራት ዓመት ይሆናል
2/ ማንኛውም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ
በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲3 መሠረት የተደረገ የጤንነት
ምርመራ ውጤት ሲቀርብና ተገቢው ክፍያ ሲፈጸም
በእያንዳንዱ ዕድሳት ወቅት ለአራት ዓመት
ይታደሳል
3/ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ባለቤት
ፈቃዱን ለፈቃድ ሰጭው አካል ራሱ ወይም
በሕጋዊ ወኪሉ አማካኝነት በማቅረብ ሊያሳድስ
ይችላል፤ ሆኖም ለሁለት ተከታታይ ጊዜ በወኪል
አማካኝነት ማሳደስ አይፈቀድም
4/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ባለቤት
ዕድሜው ከሃምሳ አምስት ዓመት በላይ ከሆነ፣
ፍቃዱ በየሁለት ዓመት መታደስ አለበት
5/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (፩) እና በዚህ አዋጅ
አንቀፅ ፲፭ (፪) መሠረት የአሽከርካሪ ፈቃዱ ቋሚ
ከሆነ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ የአገልግሎት ጊዜው
ካበቃ በኋላ ባለው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ
ሳይቀይር ወይም ሳያሳድስ የቀረ አሽከርካሪ ፍቃዱ
ቋሚ ከሆነ የተግባር ፈተና ተፈትኖ ሲያልፍ
ይታደስለታል፤ ፍቃዱ ጊዜያዊ ከሆነ ደግሞ
ከተግባር ፈተና በተጨማሪ ጊዜያዊ ፈቃዱን
በያዘበት ዓመት የተመዘገበበት የጥፋት ሪኮርድ
ታይቶ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ይታደስለታል
3/ Where an application pursuant to sub-article (2)
of this Article, is presented to the Licensing
Body, it shall issue to the applicant a
replacement driver’s qualification certification
license after the appropriate fees are discharged.
4/ A person who has recovered a driver’s
qualification certification license for which a
replacement has been issued shall promptly
submit the extra driver’s qualification
certification license to the Licensing Body for
cancellation and removal.
19. Validity and Renewal of Driver’s
Qualification Certification License
1/ A permanent driver’s qualification
certification license of any category shall be
valid for a period of four years from the date
of its issuance
2/ Any driver’s qualification certification license
shall be renewed for a period of four years, at
each time of its renewal, upon presentation of
medical examination result conducted in
accordance with Article 13 of this Proclamation
and payment of the appropriate fees.
3/ The holder of the driver’s qualification
certification license shall present his license to
the Licensing Body for renewal either in person
or through his duly authorized agent; provided,
however, that a driver’s qualification
certification license may not be presented for
renewal through an agent for two consecutive
times.
4/ Notwithstanding the provisions of sub-article
(1) of this Article, where the holder of the
driver’s qualification ratification license is
above 55 /fifty five/ years of age, the license
shall be renewed every two years.
5/ Any driver who fails to renew his license
within one year after the validity period
provided under sub-article (1) of this article
and sub article 2 of article 15 of this
proclamation has lapsed shall renew it only
upon successfully passing the practical
examination for the holder of permanent
Driver’s qualification certification license,
and upon the examination of offence record
within the year for the holder of temporary
Driver’s qualification certification license in
addition to the above requirement.